የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተናን ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተገለጸ።

64

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በ2016 የትምህርት ዘመን ስለሚሰጠው የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ፈተናን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ኀላፊዋ በመግለጫቸው ዘንድሮ 170 ሺህ 470 የ6ኛ ክፍል እና 184 ሺህ 393 የ8ኛ ክፍል በድምሩ 354 ሺህ 863 ተማሪዎች እንደሚፈተኑ አስታውቀዋል። ፈተናው የሚሰጥበት ቀን የ8ኛ ክፍል ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም ሲኾን የ6ኛ ክፍል ፈተና ደግሞ ስኔ 13 እና 14/2016 ዓ.ም መኾኑን ነው የገለጹት። ተፈታኞች የተሻለ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ በክፍል የማስተማር እና የክለሳ ሥራ መሠራቱን እንዲሁም የሞዴል ፈተና መሰጠቱን ዶክተር ሙሉነሽ ገልጸዋል።

የፈተናው አወጣጥ ምስጢራዊነቱን እና ደኅንነቱን ለመጠበቅ አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረጉን እና ከክልል እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ ግብረ ኀይል ተቋቁሞ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
ፈተናው በሰላማዊ መልኩ እንዲሰጥ እና ተፈታኞች በተረጋጋ ሁኔታ ተፈትነው ውጤት እንዲያገኙ ወላጆች እና ማኅበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ አሳሰበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጎንደር እየመከረች ነው!
Next article“በእርዳታ ስም በእጅ አዙር ዓላማቸውን ለማስፈጸም የሚፈልጉ ኀይሎችን ከተግባራቸው እንዲታቀቡ ለማድረግ ሀገራዊ አቅምን መገንባት ያስፈልጋል” ርእሰ መሥተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ (ዶ.ር)