
ባሕር ዳር: ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
የትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3/2016 እስከ ሰኔ 10/ 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት የፈተና ፕሮግራም ማውጣቱን ገልጿል።
ይሁን እንጅ ሰኔ 9/ 2016 ዓ.ም የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በመኾኑ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ወደ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም መዛዎሩን ነው የገለጸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!