
ደሴ: ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሀረሪ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ኦድሪን በድሪ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሞገስ ቸኮል እና የፌዴራል ተቋማት የሥራ ኀላፊዎች ደሴ ከተማ ገብተዋል።
የሥራ ኀላፊዎቹ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን፣ የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ፣ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሀመድአሚን የሱፍን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ኀላፊዎቹ በደሴ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ በከተማዋ ውስጥ በመገንባት ላይ ያሉ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን ተዘዋውረው እንደሚመለከቱ እና ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ አካላት ጋር ውይይት እደሚያደርጉ ተጠቁሟል።
ዘጋቢ:-ሰልሀዲን ሰይድ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!