በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የይቅርታ፣ እርቅ እና የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ።

60

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሕዝብን ሲበድሉ የነበሩ አካላት ምኅረት ተደርጎላቸዋል። በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ከጠላት ጋር ተሰልፈው ሕዝብን የበደሉ የገንቦሬ ቀበሌ ነዋሪዎች የበደሉትን ሕዝብ ይቅርታ በመጠየቅ በሕዝብ እና በመንግሥት ምኅረት ተደረጎላቸዋል።

በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የገንቦሬ ቀበሌ በጠላት ቁጥጥር የነበረች በመኾኗ አንዳንድ የቀበሌዋ ነዋሪዎች የጠላትን ዓላማ ለማስፈጸም ኅላፊነት በመውሰድ በነዋሪዎች ላይ አጸያፊ ተግባር ሲፈጽሙ ቆይተዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከክልሉ የጸጥታ ኃይሉ ጋር በቅንጅት በሠሩት ሥራ የገንቦሬ ቀበሌ ሕዝብን ከጠላት ኃይል ነጻ አውጥተዋል።

የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ አስተዳደር ነጻ በወጣችዋ ቀበሌ የቀበሌዋ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት የሰላም ኮንፈረንስ አካሄደዋል። በሰላም ኮንፈረንሱ ምኅረት የተደረገላቸው የታጣቂው ቡድን ከ15 በላይ አባላት፣ ምክትል አዛዥ ኾነው ያገለገሉ፣ የተዋጉ እና ገንዘብ በመሰብሰብ ተሰማርተው የነበሩ አባላት በሕዝብ ፊት እየቀረቡ ይቅርታ ጠይቀዋል።

በወረዳው በሚገኙ 28 ቀበሌዎች የሰላም እና የልማት ኮሚቴ ተቋቁሞ በወረዳው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ልዩ ልዩ ተግባራትን እያከናወኑ ነዉ።

መረጃዉ የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ አስተዳደር ነዉ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አረንጓዴ ልማት ያለውን ፋይዳ የተገነዘበ ማኅበረሰብ መፍጠር ያስፈልጋል።
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ልዑክ የሲንጋፖር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ልማት ጎብኝቷል።