የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አረንጓዴ ልማት ያለውን ፋይዳ የተገነዘበ ማኅበረሰብ መፍጠር ያስፈልጋል።

7

ባሕር ዳር: ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

“አረንጓዴ ልማት ለዘላቂ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ ከተማ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት ተጠሪ ኢብራሂም የሱፍ ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካባቢን ከማልማት ባሻገር በምግብ ራስን ለመቻል እና ጤናማ የሕዝብ ለሕዝብ ዲፕሎማሲ ለመመስረት ከፍተኛ አበርክቶ አለው ብለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ልማት ቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመረዳት ለዘላቂነቱ ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንደለበትም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሠይፈ ደርቤ “አረንጓዴ ልማት ለዘላቂ ብልፅግና” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው የፓናል ውይይት አስከፊ የኾነውን የአየር ንብረት ለውጥ በመቋቋም ረገድ የአረንጓዴ ልማት ያለውን ፋይዳ የተገነዘበ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ መኾኑን ገልጸዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ እና የአረንጓዴ ልማትን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሑፎች በምሁራን ቀርበው የፓናል ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎም ይጠበቃል። ውይይቱ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አሥተባባሪነት የተዘጋጀ ሲኾን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ምሁራን እና የሚዲያ ተቋማት ተሳታፊ ናቸው።

ዘጋቢ:-ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመንገድ በመዝጋት የሚመጣ መፍትሔ የለም ሲሉ የሃይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ።
Next articleበምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የይቅርታ፣ እርቅ እና የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ።