የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጎንደር ከተማ ገቡ።

63

ባሕር ዳር: ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋገሾ እና የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር እርስቱ ይርዳው የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ጎንደር ከተማ ገብተዋል። መሪዎቹ ጎንደር ከተማ ሲገቡ የአማራ ክልል መሪዎች፣ የከተማው ከንቲባ ባዩህ አቡሀይ እና ሌሎች የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከጎንደር ከተማ ኮምዩኒኬሽን መምሪያ እንዳገኘነው መረጃ መሪዎቹ በጎንደር ከተማ ቆይታቸው በከተማዋ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ። ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በሚደረጉ ውይይቶች ላይም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ ባሕር ዳር ገቡ።
Next articleመንገድ በመዝጋት የሚመጣ መፍትሔ የለም ሲሉ የሃይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ።