
ባሕር ዳር: ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር ተስፋየ ይገዙ ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።
መሪዎቹ ባሕር ዳር ሲደርሱ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ እና የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
መሪዎቹ በባሕር ዳር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ በከተማዋ ውስጥ በመገንባት ላይ ያሉ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ። በባሕር ዳር ከተማ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በሚደረገው የውይይት መድረክ ላይም እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!