
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከእስያ ጉብኝታቸው ማምሻውን በመመለስ የሶስት ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁት የሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተወካዮች ልዑክ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በቤቶች ልማት በቱሪዝም እና በግብርና በተለይም በሀገር ውስጥ የማዳበሪይ ምርት ላይ ያተኮረ ነበር።
ሰባ ዘጠኝ ኢንቨስተሮችን ያካተተው ከፍተኛ ልዑክ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) እና የሳዑዲ አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማን በሕዳር ወር በሳዑዲ – አፍሪካ ጉባኤ ወቅት ያደረጉትን የሁለትዮሽ ውይይት ተከትሎ የተከናወነ ነው።
መረጃው የጠ/ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!