
ባሕር ዳር: ግንቦት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ፣ በአባያ ቀበሌ፣ በርቅቻ ንዑስ ቀበሌ የተዘራ የበጋ መስኖ ስንዴ በዘመናዊ መንገድ እየተሰበሰበ መኾኑን የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጥላሁን እንዳላማዉ ገልጸዋል፡፡
ዘመናዊ የስንዴ መሰበሰቢያ ኮምፓይነሮችን ለአርሶ አደሮች በወቅቱ በማቅረብ የመስኖ ስንዴ እንዲሰበሰብ እያደረጉ መኾኑን የተናገሩት። በቀጣይም በዘርፉ በስፋት እንደሚሠራ ተናግረዋል። አርሶ አደሮች በበጋ መስኖ ልማት ሥራ ላይ ሰፊ ልምድ እያካበቱና የተሻለ የምርት ተጠቃሚ መኾናቸውን ተናግረዋል።
አርሶ አደሮችም በዘመናዊ መንገድ በኮምባይነር መሰብሰብ ጉልበትና ወጭ ቆጣቢ መኾኑን ነው የተናገሩት። ከዓመት ወደ ዓመት የምርት እድገት እያሳዩ የመጡና በሄክታር እስከ 72 ኩንታል ምርት እያገኙ መኾኑንም መናገራቸውን ከሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!