በገንዳውኃ ወንዝ ላይ የተሠራው ድልድይ ግንባታው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።

16

ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ጎንደር ዞን በመንገድ ቢሮ ባለቤትነት በክልሉ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ተቋራጭነት የተገነባው የገንዳውኃ አቸራ ድልድይ ተጠናቅቋል። የገንዳ ውኃ አቸራ ድልድይ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪም ተደርጎበታል። 52 ሜትር ርዝመት ያለው ፕሮጀክት መኾኑን ከክልሉ መንገድ ቢሮ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፕሮጀክቱ ገንዳውኃ ከተማን ከመተማ ወረዳ ቀበሌዎች ማለትም ዘባጭ፣ ባኃር፣ መቸላና አቸራ የተባሉ 4 ቀበሌዎችን ያገናኛል። የድልድዩ መገንባት በክረምት ወቅት በወንዝ ሙላት ምክንያት ይጠፋ የነበረ ሕይወትን፣ የሚቋረጠውን የግብይት ሂደትን፣ በወሊድ ጊዜ እናቶች ሪፈር ሲባሉ ፈጥኖ ለማድረስ የነበረውን ችግር የፈታ መኾኑም ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሰሜን ወሎ ዞን “ሰላምን በማጽናት በዘላቂነት እግር መትከል” በሚል መሪ ቃል ምክክር እየተደረገ ነው።
Next article“በጫካ የሚገኙ ወገኖችን ወደተፈጠሩበት መልካም ሥራ እንዲመለሱ ማስቻል ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ይጠበቃል” የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ