ኢትዮጵያ እና ሲንጋፖር የመግባቢያ እና የፍላጎት ስምምነት ተፈራረሙ።

35

ባሕር ዳር: ግንቦት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ልዑካቸው በሲንጋፖር ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ላይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሲንጋፖር ሪፐብሊክ በኢስታና ቤተ መንግሥት በነበራቸው ቆይታ ልዑካቸው የመግባቢያ እና የፍላጎት ስምምነት ተፈራርሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በሁለትዮሽ ምክክር ላይ የመግባቢያ ስምምነት ብሎም በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና በሲንጋፖር የትራንስፖርት ሚኒስቴር መካከል የፍላጎት ስምምነት ተፈርሟል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የተፈጥሮም ሆነ የሰው ሠራሽ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም መሥራት ያስፈልጋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ
Next articleቴሌ-ሜዲሲን