
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከተረጅነት በመላቀቅ የሚያጋጥሙ የተፈጥሮም ሆነ የሰው ሠራሽ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም መሥራት ያስፈልጋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ተናገሩ። የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በተገኙበት ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
አደጋ በየትኛውም ወቅትና ጊዜ አይቀሬ ስለመሆኑ የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር በሚያደርጉት የተዛባ ግንኙነት ቁጥሩ እየጨመረ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡ በመሆኑም አደጋን የማሥተዳደርና በራስ አቅም የመቋቋም ሥራዎች ላይ በትኩረት እየተሠራ ስለመሆኑ ነው የተናገሩት፡፡
ልመናን መፀየፍ እና የመረዳዳት እሴትን በማጎልበት በራስ አቅም ችግሮችን መቋቋም እንደሚገባም አክለው ገልፀዋል፡፡
ኢቢሲ እንደዘገበው በምክር ቤቱ ውይይት ላይ የክልል ርእሰ መሥተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የአደጋ ስጋት ኮሚሽነሮች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!