በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው ምርጫ የዴሞክራሲ መርኾዎችን ያከበረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

19

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው ምርጫ የዴሞክራሲ መርኾዎችን ያከበረ መኾኑን በመጥቀስ፤ ለፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ ፍትሐዊ፣ ግልፅ እና ሰላማዊ እንዲኾን ለሰጡት አመራር ራማፎሳን አድንቀዋል።

ይህም ፕሬዚዳንቱ ለሕዝብ ፍላጎት እና ሁሉንም ለሚያስተሳስሩት የዴሞክራሲ እሴቶች መከበር ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ አንድነት ያሻግራል፣ አንድነት ያስከብራል”
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሲንጋፖር የመጀመሪያ ቀን ጉብኝታቸው በብሔራዊው የእፅዋት ማዕከል ባህላዊውን እፅዋት የመሰየም ሥነሥርዓት ተካፍለዋል።