
ባሕር ዳር: ግንቦት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በመከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ የተመራ ልዑክ በጂቡቲ የመከላከያ ሠራዊትን 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ለመታደም ጂቡቲ ገብቷል።
ክብረ-በዓሉ ላይ የጂቡቲ የመከላከያ ሚኒስትር ሀሰን ኦመር መሐመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት አታሼዎች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት በተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች መከበሩን ከጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የማኀበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
