በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች መዳረሻቸው የት ነው?

24

ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮበኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወነው የአጀንዳ ልየታ የምክክር ምዕራፍ መድረክ አጀንዳዎች ከባለድርሻ አካላት መሰብሰባቸው ይታወቃል፡፡ ታዲያ እነዚህ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች በምን መልኩ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ይቀርባሉ?

• በምክክር ምዕራፉ ከአዲስ አበባ ከተማ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ከፌዴራል፣ ከክልሎች እንዲሁም ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ኾነው ለኮሚሽኑ ምክር ቤት ይቀርባሉ፡፡ በተመሳሳይ በሌሎች አማራጮች ከዜጎች የሚመጡ አጀንዳዎችም ለኮሚሽኑ ምክር ቤት ይቀርባሉ፡፡

• ለኮሚሽኑ ምክር ቤት የሚቀርቡትን አጀንዳዎች የኮሚሽኑ ምክር ቤት በሚያዘጋጀው አሰራር ሥርዓት መሠረት በየፈርጁ ለይቶ ያዘጋጃቸዋል፡፡

• የተዘጋጁት አጀንዳዎች ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አመቺ በኾነ መልኩ ኮሚሽኑ በመቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይቀርጻቸዋል፡፡

• ኮሚሽኑ የቀረጻቸውን የአጀንዳ ስብስቦች ለሕዝብ በማሳወቅ እና በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ተሳታፊ የሚኾኑ ባለድርሻ አካላትን በመጋበዝ የመጨረሻ የኾነውን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ያካሂዳል፡፡

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በሳዑዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ።
Next articleበብሔረሰብ አሥተዳደሩ ያለውን ሰላም ለማጽናት ከአጎራባች ዞኖች ጋር መሥራት እንደሚገባ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ነዋሪዎች ገለጹ።