በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በሳዑዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ።

31

ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በሳዑዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ሥምምነት ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈርሟል። ሥምምነቱ የተፈረመው በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኢትዮ-ሳዑዲ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ነው።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ሥምምነቱን የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፉ ማኅበራት ምክር ቤት የቦርድ አባል አይናለም አባይነህ (ዶ.ር) እና የሳዑዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሁሴን ሙጂብ (ዶ.ር) ፈርመውታል። ሳዑዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የተመራው 79 አባላትን የያዘ የሳዑዲ አረቢያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ልዑካን ቡድን ትላንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምክር ቤቶች በሕዝብ የሚነሱ ጥያቄዎች እንዲመለሱ በትኩረት መሥራት ይጠበቅባቸዋል” አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ
Next articleበአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች መዳረሻቸው የት ነው?