የሀራ ከተማ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ሰላም ዙሪያ እየመከሩ ነው።

29

ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)”ሰላምን በማጽናት በዘላቂነት እግር መትከል” በሚል መሪ መልዕክት የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኀላፊዎች ከሀራ ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው። የአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ዳይሬከተር ዛዲግ አብርሀ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) በወይይቱ ተገኝተዋል።

የሰሜን ወሎ አሥተዳደር የመንግሥት እና የብልጽግና ፓርቲ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሀራ ከተማ አሥተዳደር መሪዎች እና ነዋሪዎች የውይይቱ ተሳታፊዎች ናቸው።

ዘጋቢ፦ ካሳሁን ኃይለሚካኤል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሥራ ፈጣሪ ትውልድን ማፍራት ላይ ያለመ ውድድር በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው፡፡
Next articleየኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንደሚገኝ ተገለጸ።