በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 200 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

20

ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኦማን ማቆያ ጣቢያዎች የነበሩ 200 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን የሴቶች ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያ እና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሠራ መኾኑ ተመላክቷል፡፡

የሴቶች ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው ከሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ 1ሺህ 579 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“መነሻየን እያሰብኩ ነው የምሠራ” ባለሃብቱ በላይነህ ክንዴ
Next article“የፍትሕ ጉባኤ የፍቅር ሱባኤ…”