
ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በደቡብ ኮሪያ ሲላኦም ማዕከል ለዐይነ ስውራን ተቋምን ጎበኝተዋል።
“ዛሬ በደቡብ ኮሪያ የሚገኘውን ሲላኦም ማዕከል ለዐይነ ስውራን በተባለው ተቋም ተገኝቼ ሥራዎችን ተመልክቻለሁ” ያሉት ቀዳማዊት እመቤቷ ለዐይነ ስውራን ተማሪዎች በዘመናዊ ቴክኖዎሎጂ በመታገዝ የሚሰጡትን ስልጠናዎች እንደተመለከቱም ገልጸዋል፡፡
ከቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ እንዳገኘነው መረጃ ቀዳማዊት እመቤቷ በተቋሙ የሚሰጡ ሥልጠናዎችን በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ ከተቋሙ ኀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
 
             
  
		