
ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በሰሜን ወሎ ዞን ወረዳዎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ከወልድያ ከተማ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ውይይት እየተካሄደ ነው። ውይይቱ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ፣ ሰላም፣ ልማት እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ማዕከል ያደረገ ነው ተብሏል።
በውይይት መድረኩም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እየተሳተፉ መኾኑን ከዞኑ የመንግሥት ኮምኒኬሽን መምሪያ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
 
             
  
		