የባለድርሻ አካላት ወኪሎች አጀንዳዎችን እያደራጁ ነው።

11

ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የባለድርሻ አካላት ወኪሎች አጀንዳዎችን እያደራጁ መኾኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገልጸዋል። ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር እያስተባበረ የሚገኘው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ ለሰባተኛ ቀን እንደቀጠለ ነው።

የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች፣ ሦስቱ የመንግሥት አካላት ተወካዮች፣ የማኅበራት እና ተቋማት ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች በአምሥት ቡድኖች ተከፍለው ላለፉት ቀናት አጀንዳዎቻቸውን አስመዝግበዋል። ከአምስቱ ባለድርሻ አካላት የተመረጡ ተወካዮች ደግሞ ዛሬ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን እያደራጁ ይገኛሉ ብሏል።

ከሰዓት በኋላ በሚኖረው ክፍለ ጊዜ ደግሞ የተደራጁት አጀንዳዎች ለጉባኤው ይቀርቡና ምክክር ይደረግባቸዋል፡፡ በዚህ ምክክር የሚደራጁት አጀንዳዎች የአዲስ አበባ ከተማ የምክክር ምዕራፍ ውጤት እንደሚሆኑ ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የቢዝነስ የልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው።
Next articleበከተማ ግብርና ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መኾኑን የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።