ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ፊቤላ ኢንዱስትሪያል የደብረ ብርሃን መኪና መገጣጠሚያን መረቁ።

87

ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ከተማ በባለሃብቱ በላይነህ ክንዴ የተገነባው ፊቤላ ኢንዱስትሪያል የደብረ ብርሃን መኪና መገጣጠሚያ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎችም የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ መሪዎች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።

ፋብሪካው ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ የተገነባ ሲኾን በተለይም በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ያመርታል። በዚህም ከ1 ሺህ በላይ ለኾኑ ዜጎች የሥራ እድል የፈጠረ መኾኑም ተጠቁሟል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleእየዘመነ የመጣው የንብ ማነብ ሥራ!
Next articleኢትዮጵያ ከደቡብ ኮሪያ ልምድ መውሰዷ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገለጹ።