
አዲስ አበባ: ግንቦት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሁለተኛው የኢትዮጵያ እና ምሥራቅ አፍሪካ ስታርት አፕ ውድድር ሽልማት የዓለምአቀፉ ስታርት አፕ ሽልማት ተወካዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ለሀገር እድገት ትልቅ አበርክቶ ያለውን የስታርት አፕ ሥነ ምህዳር ለማልማት መንግሥት በትኩረት እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል። በዚህም ትልቅ ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ያሉት።
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ኢትዮጵያ መገንባት የምትፈልገውን ፈጠራ መር ኢኮኖሚ እውን ለማድረግ ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ባሕል ማድረግ ይገባል ብለዋል። በአህጉር አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ወክለው በ2024ቱ ዓለምአቀፍ የስታርት አፕ ውድድር 731 የኢትዮጵያ ስታርት አፖች በውድድሩ መሳተፋቸውም ተገልጿል። 68ቱ አሸናፊ ኾነው ተለይተዋል። እነዚህ አሸናፊ ስታርት አፓች በአህጉርአቀፍ እና ዓለምአቀፉ የ2024ቱ የስታርት አፕ ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
መድረኩን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲኹም የኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት በጋራ አዘጋጅተውታል።
ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
