የአምስት ትልልቅ ስኳር ፋብሪካዎች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ እና የተሻለ ሥራ እንዲሠሩ ለማድረግ ሲካሄድ ከቆየው የአዋጭነት ጥናት የአንዱ መጠናቀቁ ተገለጸ።

28

ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የከሰም ስኳር ፋብሪካ የአዋጭነት ጥናት ሰነድን አጠናቅቆ አስረክቧል። የጥናት ሰነዱን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ሥራ አሥኪያጅ ሽፈራው ሰለሞን ለከሰም ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ታፈሰ ሻታ አስረክበዋል።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት ትልልቅ ስኳር ፋብሪካዎች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ እና የተሻለ ሥራ እንዲሠሩ ለማድረግ ያለመ የአዋጭነት ጥናት ለመሥራት ውል በመፈጸም ሢሠራ መቆየቱን በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል። ከእነዚህም ውስጥ የ3 ስኳር ፋብሪካዎች ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለአስተያየት መላኩን እና የከሰም ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ማስረከባቸውን ነው የተናገሩት።

አቶ ሽፈራው ስኳር ፋብሪካው በተሠራው ጥናት እና ግኝት ተመስርቶ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንደሚገባ ሙሉ እምነት አለን ማለታቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላታክል። የከሰም ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ታፈሰ ሻታ የተሠራው የአዋጭነት ጥናት የስኳር ፋብሪካው በመሉ አቅም ወደ ሥራ እንዲገባ እና በአጭር ጊዜ ወደ ትርፋማነት እንዲመለስ እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየታዳሽ ኢነርጂ ሃብቶችን በመጠቀም በአፍሪካ የማይበገር የኢንዱስትሪ እና ኢኮኖሚ እድገት መገንባት እንደሚቻል ተጠቆመ።
Next article“መንግሥት የስታርት አፕ ሥነ ምህዳሩን ለማልማት በትኩረት ይሠራል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ