
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው የምክክር ምዕራፍ ሂደት ውስጥ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ተሳታፊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ለመኾኑ እነዚኽ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች የትኞቹን አካላት ወክለው እየተሳፉ ይገኛሉ?
1. የሕብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች
• ከየወረዳው የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን እንዲወክሉ የተመረጡ ተወካዮች
2. የፓለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች
• በአዲስ አበባ ከተማ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ የፓለቲካ ፓርቲዎች
3. የተቋማት እና ማኀበራት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ)
• የሃይማኖት ተቋማት
• ሲቪል ማኀበራት
• የአሰሪዎች ማኀበራት
• የሰራተኞች ማኀበራት ኮንፌዴሬሽን
• የመምህራን ማኀበር
• የአካል ጉዳተኞች ማኀበራት
• የሙያ ማኀበራት
• የቀድማው ሰራዊት ማኀበር (ተቀናሽ ሰራዊት ማኀበር)
• የጋዜጠኞች ማኀበር
• የዩኒቨርሲቲ መምህራን (የመንግስት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት)
• የንግድ ማኀበራት ምክር ቤት
• የሴቶች እና ወጣቶች ማኀበራት
4. የመንግስት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለው ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈፃሚ እና ሕግ ተርጓሚ)
• የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር
• የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት
• የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች
• የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች
• የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን
5. ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች
• በተለያዩ ዘርፎች በሕዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያላቸው፣ አንቱታን ያተረፉ እና ተፅእኖን መፍጠር የሚችሉ ግለሰቦች
ኢትዮጵያ እየመከረች!
