
ወልድያ: ግንቦት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላምን በማጽናት በዘላቂነት እግር መትከል” በሚል መሪ መልእክት የሰሜን ወሎ ዞን እና የወልድያ ከተማ አሥተዳደር የመሪዎች ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
የአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ዳይሬከተር ዛዲግ አብርሀ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) በውይይቱ ተገኝተዋል። የሰሜን ወሎ እና የወልድያ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት እና የብልጽግና ፓርቲ ኀላፊዎች የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች የውይይቱ ተሳታፊዎች ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!