
ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት እና ጉድ ኔበርስ ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈርው መልዕክት ዋናው መቀመጫው እና የተመሠረተበት ሀገር ደቡብ ኮሪያ የኾነው ጉድ ኔበርስ ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ባስተላለፉት መልእክትም ጉድ ኔቨርስ በጽሕፈት ቤታችን እየተከናወኑ ያሉትን የልማት ሥራዎች ለመደገፍ እና በጋር ለመሥራት የሚያስችለንን ውይይት አድርገናል ብለዋል። በውይይቱም ወደ ሥራ የሚያስገባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውንም ቀዳማዊት እመቤቷ ተናግረዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!