“በጀመርነው የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሐ ግብር በኩል መጻሕፍትን በቀላል መንገድ ለማዳረስ እንሠራለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

21

ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ማንበብ ባሕል መጻሕፍትም ቤተኛ እንዲሆኑ እንደ ሀገር መሥራት አለብን ብለዋል። የሰከነ፣ የሚያሰላስልና በሐሳብ ልዕልና የሚያምን ማኅበረሰብ ለመገንባት ንባብ ወሳኝ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት።

የንባብን ባህል ለመገንባት ወሳኝ የሆኑትን አብያተ መጻሕፍት፣ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየገነባን ነው ብለዋል። በጀመርነው የዲጂታል ኢትዮጵያ መርሐ ግብር በኩል መጻሕፍትን በቀላል መንገድ ለማዳረስ እንሠራለን ነው ያሉት። “የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በኩል በ2016 ለ አንድ መቶ ቀናት ንባብን ሲያበረታታ ቆይቷል። ሌሎች ሚዲያዎችም በተመሳሳይ መንገድ ንባብን እንዲያበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ።” ብለዋል።

መጪው ክረምት ነው። ብዙ ወጣቶች ዕረፍት ላይ ይሆናሉ። ጊዜያቸውን በንባብና በበጎ ፈቃድ” አገልግሎት እንዲያሳልፉ በብርቱ ልንሠራ ይገባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ•ር)።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመሪዎች ከኅብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የሠሩት ሥራ በአርዓያነት የሚወሰድ መኾኑ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሀ ደሳለኝ ገለጹ።
Next articleበጸጥታ ችግር እየተፈኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች!