
ደብረ ብርሃን: ግንቦት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በደብረብርሃን ከተማ በእትጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ልቼ ቀበሌ ከ 11 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባው የቢሮ እና የመሠብሠቢያ አዳራሽ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሀ ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል።
የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት የቢሮ እና የመሠብሠቢያ አዳራሹ በአጭር ጊዜ ተገንብቶ አገልግሎት እንዲሰጥ የአካባቢው ኅብረተሰብ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እና በዕውቁቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምሥጋና አቅርበዋል።
የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሀ ደሳለኝ ኅብረተሰቡ እና መሪዎች ከተደማመጡ እና ከተግባቡ ውጤታማ መኾን እንደሚቻል በልቼ ቀበሌ የተገነባው የቢሮ እና የመሠብሠቢያ አዳራሽ ማሳያ ይኾናል ብለዋል።
የቢሮ እና የመሠብሠቢያ አዳራሹ ግንባታ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የሰላም ቱርፋት ነው ያሉት አቶ ፍስሀ ሕዝቡን መሰል የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ሰላምን መጠበቅ እና መንከባከብ የሁሉም ዜጋ ኀላፊነት ሊኾን እንደሚገባ አሳስበዋል።
የቢሮ እና የመሠብሠቢያ አዳራሹን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ስድስት ወራት ብቻ መፍጀቱም ተገልጿል።
ዘጋቢ፦ ፋንታነሽ መሐመድ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!