
ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ስለሚገኘው የምክክር ምዕራፍ አንኳር ነጥቦችን ይፋ አደረገ።
ባሕር ዳር: ግንቦት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ስለሚገኘው የምክክር ምዕራፍ አንኳር ነጥቦችን ይፋ አድርጓል።
ነጥቦቹ👇
👉 በአዲስ አበባ ከተማ 11 የኅብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ 2000 የኅብረተሰብ ወኪሎች በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም በተደረገው የተሳታፊዎች ልየታ እና ተወካዮች መረጣ ላይ ተመረጡ፡፡
👉 11 የኅብረተሰብ ክፍሎች የምንላቸው፡-
ራሳቸውን የሚገልፁበት መተዳዳሪያ ያላቸው (አርሶ አደሮች ወይም አርብቶ አደሮች)፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ እድሮች፣ የማኅበረሰብ መሪዎች (እናቶች፣ አባቶች)፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የግል ድርጅት ሠራተኞች፣ መምህራን፣ በባሕልና በሙያቸው ምክንያት የተገለሉ ተፈናቃዮች ናቸው፡፡
👉 11 በከተማዋ የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ 2000 ተሳታፊዎች ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ቀን በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ ተገኝተው የምክክር ምዕራፋቸውን በይፋ ጀመሩ፡፡
👉 እነዚህ 11 የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ከግንቦት 21ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት ጀምሮ ወደ ግዮን ሆቴል በመዛወር እስከ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በ22 ቡድን ተከፍለው በአጀንዳ ሀሳቦቻቸው ላይ በጋራ ተወያየተው እና ተስማምተው የአጀንዳ ሀሳቦቻቸውን በቃለ-ጉባኤ አፀደቁ፡፡
👉 ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም በትይዩ ኮሚሽኑ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ በከተማዋ ለሚገኙ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ስለ ምክክር ምዕራፍ ሂደት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ፡፡ በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ የፓለቲካ ፓርቲዎች ፣ የሶስቱ የመንግስት አካላት ተወካዮች (ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና ሕግ ተርጓሚ) የተቋማትና የማህበራት ተወካዮች እንዲሁም የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
👉 በግዮን ሆቴል ሲመክሩ የነበሩ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በቀጣዮቹ የምክክር መድረኮች (ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በሚኖረው የምክክር ሂደት) የአጃንዳ ሀሳቦቻቸው እንዲንፀባረቅላቸው እያንዳንዳቸው 11 ተወካዮችን በመምረጥ በአጠቃላይ 121 ተወካዮችን መርጠው ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም የአጀንዳ ሀሳቦቻቸውን ለወኪሎቻቸው በአደራ ሰጥተዋል፡፡
👉 የተመረጡት 121 የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ከሌሎች አራት የባለድርሻ አካላት ወኪሎች በየግላቸው በቡድን (የፓለቲካ ፓርቲዎች ፣ ከሶስቱ የመንግስት አካላት ተወካዮች (ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና ሕግ ተርጓሚ) የተቋማትና ማኅበራት ተወካዮች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች) በአጀንዳ ሀሳቦቻቸው ላይ ከዛሬ ግንቦት 25/2016 ዓ.ም ጀምሮ የቡድን ውይይቶችን ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ከዚህ የውይይት መድረክ ( በቀጣዩቹ ቀናት) ሁሉም የሚገናኙበት የጋራ መድረክ ይዘጋጅና የአጀንዳ ሀሳቦቻቸውን በጋራ ሆነው ያደራጃሉ፡፡
#በመሆኑም፦
የሕብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች (121)
👉 መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ማኅበራት ተወካዮች
👉 ከሶስቱ የመንግሰት አካላት የተውጣጡ ወኪሎች
👉 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች
👉 የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች እስከ ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም በጋራ ውይይቶችን በማድረግ የአጀንዳ ሀሳቦቻቸውን ካዘጋጁ በኋላ እያንዳንዳቸው ለቀጣዮቹ የምክክር ምዕራፎች የሚወክሏቸውን አምስት አምስት ተወካዮችን በአጠቃላይ 25 ተወካዮችን የሚመርጡ ይሆናል፡፡
👉 በባለድርሻ አካላቱ የሚመረጡት እነዚህ 25 ተወካዮች ከወከሏቸው አካላት ያመጧቸውን የአጀንዳ ሀሳቦች በጋራ ሆነው ያደራጃሉ፤ ያደራጁትን አጀንዳ ለምልዓተ ጉባኤው (የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ለሚሳተፉበት መድረክ) ያቀርባሉ፡፡
👉 በዚህ ሂደት እነዚህ ወኪሎች የአጀንዳ ሀሳቦቹን ሲያደራጁ አስፈላጊነትን፣ አስቸኳይነትን እና ወካይነትን ከግምት እንዲያስገቡ ይጠበቃል፡፡
👉 በዚህ ሂደት የተደራጁ የአጀንዳ ሀሳቦች የአዲስ አበባ ከተማ አጀንዳ ይሆናሉ፡፡
👉 ይህም ሂደት የከተማይቱ የመጨረሻው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይሆናል፡፡
👉 ከላይ የተመረጡት 25 የባለድርሻ አካላት ወኪሎች አዲስ አበባ ከተማን በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ የሚወክሉ እንደሚኾን ከኮሚሽኑ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!