ጦርነትን ኖረንበታል። የተወሰኑ ችግሮቻችንን ፈትተንበታል።

41

አብዮትን ደጋግመነዋል። የተወሰኑ ችግሮችን ፈትተንበታል።

በሁለቱም ያልተፈቱትን ችግሮች ለመፍታት የቀረን መንገድ ምክክር ነው።

ምክክርን ግን አልተጠቀምንበትም።

ጦርነትና አብዮት የተሟላ መፍትሔ የማያመጡት አሸናፊ እና ተሸናፊ ስለሚያስከትሉ ነው።

ቢዘገይም የተሸነፈው ለማሸነፍ ይታገላል። ያሸነፈውም ድሉን ለመጠበቅ ይዋጋል።

ምክክር ግን ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል። ከተሸነፍንም ሁላችንም ለሀገራችን ብለን ነው የምንሸነፈው።

ይሄ የምክክር ሂደት ሦስት ነገሮች ያስገኝልናል።

1. ሁሉንም ባይሆን እንኳን ዋና ዋና ችግሮችን ይፈታል
2. ከጦርነት ይልቅ ምክክር ባህል እንዲሆን ያደርጋል
3. በተቃራኒ ኃይሎች መካከል መቀራረብና መግባባት ይፈጥራል።

ይሄንን መቀራረብ በመጠቀምም ወደፊት በጉዳዮች እየተነጋገርን ለመቀጠል ያስችለናል። በመሆኑም ይኽንን እድል ሳናበላሽ ወደ ተሟላ ድል እንድናሸጋግረው እጠይቃለው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

Previous articleለጽዳት የወጣው ሕዝብ ከተማዋ በልማት ጎዳና ላይ እየተራመደች መኾኑ እና አስተማማኝ ሰላም በከተማዋ መኖሩ ማሳያ እንደኾነ ተገለጸ፡፡
Next articleሰላምን ለማጽናት ታሳቢ ያደረገ ሕዝባዊ ውይይት በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር እየተካሄደ ነው።