“ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር የሰላም እና የልማት ሥራዎችን በቁርጠኝነት መሥራት ይገባል” ደሳለኝ ጣሰው

106

ባሕር ዳር: ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አሥተባባሪ እና የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው፣ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ መሪዎች በተገኙበት በቀጣይ 100 ቀናት በሚከናወኑ የፖለቲካ፣ የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ላይ በጎንደር ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አሥተባባሪ እና የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው አሁን ላይ ያለውን አንጻራዊ ሰላም በዘላቂነት በማጽናት የሰላም፣ የልማት፣ የፖለቲካ እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን በቀጣይ ቀሪ ጊዜያት በቁርጠኝነት መሥራት ይገባል ብለዋል።

በውጤት የሚለካ የአሠራር ሥርዓት በመፍጠር ኅብረተሰቡን ከችግር የሚያወጣ ሥራ ማከናወን እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የመሬት መምሪያ ኀላፊ አላምረው አበራ ባለፉት ጊዜያት በችግር ውስጥ በሰላም እና ልማት ሥራዎች ዙሪያ አበረታች ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አንስተዋል።

በቀጣይ ቀሪ ጊዜ ያልተከናወኑ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን አቅዶ እና አቀናጅቶ መፈጸም እንደሚገባም ነው የተናገሩት። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው በመድረኩ የቀጣይ 100 ቀናት ዕቅዱ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ካሳሁን ንጉሴ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የምክክር ምዕራፍ በዕቅዱ መሰረት እየተከናወነ መሆኑን ኮሚሽኑ ገለጸ።
Next articleምክክሩ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ወሳኝ በመኾኑ መደገፍ አስፈላጊ መኾኑን ዩኒቨርሲቲዎች ገለጹ።