ሴቶች ለሰላም መስፈን ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።

12

ባሕር ዳር: ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)

ከሰላም መደፍረስ ጋር ተያይዞ የሴቶችን የጥቃት ተጋላጭነት ለመከላከል ኅብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሴቶች ሕጻናት ማኅራዊ ጉዳይ መምሪያ አሳስቧል፡፡ በግጭት ሁኔታዎች ውስጥ ሴቶች ለጾታዊ ጥቃት የበለጠ የተጋለጡ ናቸው። ችግሩን ለመቀነስ ሴቶች ስለ ሰላም መስፈን መምከር የሚችሉበት ዕድል አላቸው፡፡

ሴቶች ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አሁን ላይ ለሰላም እና መረጋጋት መሥራት እንዳለባቸው የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሴቶች ሕጻናት ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ አሞኘሽ መሃመድ ገልጸዋል፡፡ ኀላፊዋ በዞኑ ባጋጠመው ግጭት በርካታ ሴቶች ለጥቃት መጋለጣቸውን ጠቅሰው ችግሩን መቀነስ የሚቻለው ሴቶች ስለ ሰላም መምከር እና መነጋገር ሲችሉ መኾኑን ተናግረዋል፡፡

በየደረጃው ያለመሪ ሴቶች ስለ ሰላም የሚመክሩበትን ምቹ ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የነጻነት ፊታውራሪ፣ እናት ሀገር አስከባሪ”
Next articleየለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ማምረት ሊገባ ነው፡፡