“ለሀገር የሚጠቅም ትክክለኛ ምክክር ማድረግ ይጠበቅብናል” ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

18

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው። በከተማ አስተዳደር ደረጃ በመድረኩ ለተወከሉ ከ1 ሺህ 200 በላይ ባለድርሻ አካላት ስለምክክር ሂደቱ ትምህርት እየተሰጠ ነው።

በመድረኩ የሃይማኖት ተቋማት፣ የመምህራን ማኀበር፣ የሲቪል ማኀበራት፣ ክልላዊ እና የሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ መኾኑ ተገልጿል። በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበርን ጨምሮ ለምክክሩ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ኢቢሲ እንደዘገበው ለምክክሩ መሳካት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የተለያዩ አካላት ዋጋ ከፍለዋል ያሉት ዋና ኮሚሽነሩ እኛም የሁሉንም ልፋት በሚመጥን ልክ ለሀገር የሚጠቅም ትክክለኛ ምክክር ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት የሚኖረው አብዛኛው ሕዝብ በሀገሩ ጉዳይ ላይ ተቀራርቦ መሥራት ሲችል ነው” ምክትል አፈጉባኤ እታፈራሁ ተሰማ
Next articleለሀገራዊ ምክክሩ የኅብረተሰብ ክፍል ወኪሎች አጀንዳዎቻቸውን በቃለ ጉባኤ እያደራጁ ነው፡፡