“ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት የሚኖረው አብዛኛው ሕዝብ በሀገሩ ጉዳይ ላይ ተቀራርቦ መሥራት ሲችል ነው” ምክትል አፈጉባኤ እታፈራሁ ተሰማ

9

ደብረ ብርሃን፡ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ሀገራዊ ማንነት እና ሀገራዊ እሴቶች ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ምስረታ ” በሚል መሪ መልዕክት የደብረብርሃን ከተማ ምክር ቤት የሰላም የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው። የደብረብርሃን ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ እታፈራሁ ተሰማ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት የሚኖረው አብዛኛው ሕዝብ በሀገሩ ጉዳይ ላይ ተቀራራቦ መሥራት ሲችል ነው ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያውያን በፍቅር እና በመቻቻል ያቆዩትን መልካም እሴት ጠብቆ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል። በዘላቂነት ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ሥራዎችን መሥራት እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ደግሞ በከተማው ምክር ቤት የበጀት እና ፋይናንስ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ የኔአንተ አለኸኝ ናቸው።

የደብረ ብርሃን ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ መንግሥቱ ቤተ፣ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት፣ የደብረ ብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሰለሞን ጌታቸውን ጨምሮ ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በመድረኩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከ60 እስከ 70 ከመቶ የሚኾኑት ግጭቶችን በሀገር በቀል የግጭት መፍቻ መንገድ በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ይቻላል።

ዘጋቢ፦ ገንዘብ ታደሰ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአረንጓዴ ልማት ስፍራዎችን ለማስፋፋት ማነቆ የኾኑ አሠራሮችን መፍታት ይገባል” አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)
Next article“ለሀገር የሚጠቅም ትክክለኛ ምክክር ማድረግ ይጠበቅብናል” ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ