
ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ሀሰንአገር እና ቦርከና ክፍለ ከተሞች እየተካሄዱ ያሉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ሳይት ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር ተገኝተን ተመልክተናል ብለዋል።
በሰላም ወዳዱ ሕዝብ፣ በአመራሩ እና ፀጥታ መዋቅሩ ቅንጅት ፕሮጀክቶችን በምሽት ጭምር በከፍተኛ ሞራል ሲያካሂዱ ተመልክተናል ብለዋል ዶክተር አሕመዲን። ፕሮጀክቶቹን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እና ጥራት ለማጠናቀቅ እየሠሩ ሲኾን የተስተዋሉ ችግሮችን በቦታዉ በመገፕት መፍትሔ ተሰጥቷል ነው ያሉት።
ዶክተር አሕመዲን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በምሽት ፕሮጀክቶችን የመከወን ልምድ በውስን ከተሞች እየተሠራ ቢኾንም በሁሉም ከተሞቻችን የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!