
ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፓኪስታኑ ሲያልኮት ንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የኤክስፖርት ስታንዳርድ ያላቸውን የስፖርት ግብዓቶችን ለማምረት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ተፈራርሟል። የሲያልኮት ንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አብዱል ጋፉር እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሃና አርያስላሴ ናቸው የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት።
በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር እና በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት የመግባቢያ ስምምነቱ ሲፈረም ተገኝተዋል። ሁነቱ ሁለቱ ሀገራት በመካከላቸው ያለውን ንግድ እና ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መኾኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!