በነባሩ ጭልጋ ወረዳ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ በጫካ የነበሩ ታጣቂ ኃይሎች ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቀሉ።

22

ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በነባሩ ጭልጋ ወረዳ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ በጫካ የነበሩ ታጣቂ ኀይሎች ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቅለዋል።

የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተቀላቀሉ አካላት በሙሉ አቅማቸው ወደ ልማት እንደሚሰማሩ ተናግረዋል። ለተደረገላቸው የሰላም ጥሪ መንግሥትን አመስግነው በቀጣይ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው መደበኛ ሥራቸውን እንደሚጀምሩም ነው የገለጹት። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ መረጃ እንደሚያመላክተው ሌሎች አካላትም መንግሥት ያመቻቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እንዲገቡ ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉ ታጣቂዎች ጥሪ አቅርበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የድንች ቀን እየተከበረ ነው።
Next articleየፓኪስታን ባለሃብቶች በኢትዮዽያ በጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ።