ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የድንች ቀን እየተከበረ ነው።

15

ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዛሬን ቀን (May 30) ዓለም አቀፍ የድንች ቀን ተብሎ እንዲከበር የወሰነዉ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ነው። ስለዚህ ይኽ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የድንች ቀን መኾኑ ነው።

ድርጅቱ ይኽን የወሰነው ድንች ረሀብን ከማጥፋት፣ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ከማሳደግ አኳያ ለዓለም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላለው ነው። በመኾኑም ቀኑን በዚህ መልክ መዘከር በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ ድንች ያለን ግንዛቤ ያሳድጋል ብሎ ያምናል። ለ2030 አጀንዳ፣ ቀጣይነት ያለው ልማት የማረጋገጥ አጀንዳ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ስለ ድንች ምን ያህል ያውቃሉ?

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚከተሉትን ሳይንሳዊ እውነታዎች ያስቀምጣል።

👉 67 በመቶ የሚኾነው የዓለማችን ሕዝብ ድንችን የዘወትር ምግብ አድርጎ ይመገበዋል።

👉 ድንች ከስንዴ፣ በቆሎ እና ሩዝ ቀጥሎ በዓለም ላይ በስፋት ከሚመረቱ ምርቶች የአራተኛነትን ደረጃ ይይዛል። እስካሁን ባሉት ሳይንሳዊ ጥናቶች አምስት ሺህ የድንች ዝርያዎች ይገኛሉ።

👉 ድንች በድርቅ፣ በቅዝቃዜ እና ለም ባልኾነ መሬት ላይ መልማት ይችላል። በየትኛውም የአየር ሁኔታ ጋር ተስማሚ የኾነ እህል ነው።

👉 ድንች በንጥረ-ነገሮች የበለጸገ ሲኾን በተለይ በቂ የተፈጥሮ ሃብት በሌለባቸው ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቀሉ።
Next articleበነባሩ ጭልጋ ወረዳ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ በጫካ የነበሩ ታጣቂ ኃይሎች ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቀሉ።