“በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሠራ ነው” ከንቲባ መሐመድአሚን የሱፍ

18

ደሴ: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በከተማ አሥተዳደሩ ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ለ10 ቀናት የሚቆይ ሀገር አቀፍ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ተከፍቷል። በባዛሩ ላይ በከተማዋ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ለኅብረተሰቡ በስፋት መቅረባቸውን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ኑሩ ሰይድ ተናግረዋል።

የመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች በስፋት መቅረቡን የገለጹት ኀላፊው ይህም ኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበያይ ያስችላል ነው ያሉት። የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሀመድአሚን የሱፍ ሀገር አቀፍ የንግድ ትርኢት እና ባዛሩ የከተማውን ሰላም ለማሳየት እና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ታስቦ የተዘጋጀ መኾኑን አንስተዋል።

አምራቾችም ምርታቸውን በቀጥታ ለተጠቃሚው ማኅበረሰብ በማቅረብ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስለመኾኑ ገልጸዋል። በባዛሩ ላይ ከ90 በላይ ባለሃብቶች ምርታቸውን ለተጠቃሚው ማኅበረሰብ ማቅረባቸውንም ከንቲባው ገልጸዋል። ከተማ አሥተዳደሩም ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት እየተሠራ መኾኑንም ከንቲባ መሐመድአሚን ጠቅሰዋል።

ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየማኅበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ቤት መከፈቱ ጤንነታቸውን ለመጠበቅ እንዳገዛቸው የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next articleየፈተና ጥሪ ማስታወቂያ