
ደሴ: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከተማ ልማት ዘርፍ በትራንስፖርት፣ ሎጄስቲክስ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) እንዲሁም የክልል እና የከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) “ከተሞችን ጽዱ እና ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ በቅንጅት እየተሠራ ነው” ብለዋል። በክልሉ መሬት የወሰዱ ባለሃብቶችም በውላቸው መሰረት ወደ ሥራ እንዲገቡ ድጋፍ እየተደረገ መኾኑን ጠቁመዋል። በውላቸው መሰረት ወደ ልማት በማይገቡ ባለሃብቶች ላይ ደግሞ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በአውደ ጥናቱ፣ የአማራ ክልል የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በፍኖተ ካርታ የተቃኘ የኢንቨስትመንት ፍሰት ማሳለጥ፣ የጣና መቀነት የኢንቨስትመንት ቀጣና ልማት ጥናት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ የአካባቢ ጽዳት ንቅናቄን በተመለከተ ውይይት እየተደረገ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!