የኅብረተሰብ ተወካዮች በአጀንዳ ሃሳቦች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

17

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሁለተኛ ቀኑን ያስቆጠረው እና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ እያስተባበረ የሚገኘው የምክክር ምዕራፍ ዛሬም ቀጥሏል፡፡ ከግንቦት 21/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በነበረው መርሐ ግብር ተሳታፊዎች በየኅብረተሰብ ክፍላቸው በቡድን በመኾን ከወከላቸው ማኅበረሰብ በአደራ ባመጧቸው የአጀንዳ ሃሳቦች ላይ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በሂደቱ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የኛ የሚሉትን እና የተስማሙባቸውን የአጀንዳ ሃሳቦች በማጠናከር ለኮሚሽኑ በቃለ ጉባኤ ተፈራርመው የሚያቀርቡ ይኾናል፡፡ እነዚህ የአጀንዳ ሃሳቦችም በቀጣዮቹ ቀናት በሚኖሩ መድረኮች በተወካዮቻቸው አማካኝነት ይቀርባሉ፡፡ ዛሬ ከሰዓት በሚኖረው መርሐ ግብርም ተሰብሳቢዎች በቀጣዮቹ የምክክር ምዕራፎች ላይ የሚወከሏቸውን 121 ተወካዮች በመምረጥ ለሚቀጥሉት የምክክር ምዕራፎች ይዘጋጃሉ፡፡

ኮሚሽኑ እያስተባበረ የሚቆየው ይህ የምክክር ምዕራፍ በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ የአራት ባለድርሻ አካላት ተወካዮችን በማሳተፍ እንደሚቀጥል ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ያዘጋጀው 2ኛው ቢግ 5 የግንባታ አውደ ርዕይ ተጀመረ።
Next articleበጎንጂ ቆለላ ወረዳ በፀጥታ ኃይሉ እና በኅብረተሰቡ ተሳትፎ አንጻራዊ ሰላም መገኘቱ ተገለጸ።