
ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከዲ ኤም ጂ ኤቨንት ጋር በመኾን ያዘጋጀው 2ኛው ቢግ 5 የግንባታ አውደ ርዕይ ተጀምሯል። “ኢትዮጵያን እንገንባ” በሚል በሚሊኒየም አዳራሽ የተጀመረው ግዙፍ ዓለም አቀፍ የግንባታ አውደ ርዕይ ለሦስት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል። አውደ ርዕዩ የሀገሪቱን የግንባታ ዘርፍ ለዓለም ማስተዋወቅ እና ተወዳዳሪ ማድረግ ዓላማ ያደረገ ነው።
በቢግ 5 ዓለም አቀፍ የግንባታ አውደ ርዕይ የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት ሽግግር የሚደረግበት መኾኑን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል። ሁነቱ በኢትዮጵያ መዘጋጀቱ ዘርፉን ለማነቃቃት፣ ያለውን እምቅ አቅም ለማስተዋወቅ፣ የዘርፉን ማነቆዎች ለመፍታት የሚያግዙ ውይይቶችን ለማድረግ፣ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮን ለመጋራት እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች ያሉት መድረክ ነው ሲሉ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
157 አውደ ርዕይ አቅራቢዎች፣ ከ20 በላይ ሀገራት ተሳታፊዎች እና ከ9 ሺህ በላይ ጎብኝዎች እንደሚገኙበት ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡- ድልነሳ መንግሥቴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!