“ኢትዮጵያ እያደገ በመጣው የግንባታ ዘርፍ ለያዘችው 10 ዓመት ዕቅድ ስኬት የውጭ አጋሮች ጋር አብራ መሥራት ትፈልጋለች” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

35

አዲስ አበባ: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የቢግ 5 የኮንስትራክሽን ኤግዚቪሽን አስጀምረዋል። የኮንሥትራክሽን ዘርፉ ዕድገት 54 ነጥብ 4 ቢሊዮን የነበረ ሲሆን በቀጣይ ከዚህ ከፍ ያለ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።

መንግሥት የዘርፉን ዕድገት ለማበረታታት ከቀረጥ ነጻ ማሽነሪዎችና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ለማስገባት የሚያስችል ፖሊሲዎችን ለማውጣት እየሠራ ነው ብለዋል። ለቤት ልማት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ መንግሥት ላቀዳቸው ታላላቅ የሪል እስቴት ፕሮጀክቶችም አጋዥ ሚናን እንደሚጫወት ጠቅሰዋል።
ሁነቱ በፍጥነት እያደገ ያለውን የግንባታ ገበያ ክፍተት ለመሙላት ያግዛልም ተብሏል።

መድረኩ የተለያዩ የፓናል ውይይቶች በጎንዮሽ የሚደረጉበት ይሆናል። የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመክፈቻው ተገኝተዋል።

ዘጋቢ:–ድልነሳ መንግሥቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“3 ነጥብ 023 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ቀርቧል” የማዕድን ሚኒስቴር
Next articleአማራጭ ወደብ ለማግኘት በሚያስችሉ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት እየተካሄደ ነው።