“3 ነጥብ 023 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ቀርቧል” የማዕድን ሚኒስቴር

20

ባሕር ዳር: ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ29ኛ መደበኛ ስብሰባው የማዕድን ሚኒስቴርን የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እያዳመጠ ነው፡፡ የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ.ር) በበጀት ዓመቱ የወጪ ማዕድናት ምርትን በስፋትና በጥራት በማምረት ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ማሳደግ ላይ በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

በኩባንያዎች 2 ነጥብ 414 ቶን እንዲሁም በባህላዊ 0 ነጥብ 609 ቶን በአጠቃላይ 3 ነጥብ 023 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡን አንስተዋል፡፡ በዚህም 274 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡ ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 83 በመቶ ብልጫ እንዳለው መናገራቸውንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ በታዳጊ ሀገራት ፍትሐዊ እና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማቅረብ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበች።
Next article“ኢትዮጵያ እያደገ በመጣው የግንባታ ዘርፍ ለያዘችው 10 ዓመት ዕቅድ ስኬት የውጭ አጋሮች ጋር አብራ መሥራት ትፈልጋለች” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ