
ባሕር ዳር: ግንቦት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በስሩ ከሚተዳደሩ ካምፓኒዎች ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት በካምፓኒዎች መፈፀም ስላለባቸው የኦዲት፣ የትርፍ ድርሻ ክፍያ እና ከሆልዲንጉ ጋር ባለው የሥራ ግንኙነት ሥለነበሩ መልካም አፈፃፀሞች መወያየታቸውን አመላክተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ፈጥነን በጋራ መፍታት እና መሻገር ስለሚገቡን ተግዳሮቶች ምክክር አድርገን ተግባብተናል” ሲሉም ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!