አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከኒውዝላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።

34

ባሕር ዳር: ግንቦት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከኒውዝላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊኒስተን ፒተር ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች እንዲሁም በሰብዓዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ያተኮረ እንደነበር ተመላክቷል።

በተጨማሪም የጋራ ፍላጎትን መሰረት ባደረጉ የሁለትዮሽ፣ አሕጉራዊ እና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መኾኑንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተቋማት የሚይዙት በጀት ሀገሪቱ በራሷ አቅም የምታሟላው እና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መኾን እንዳለበት የቋሚ ኮሚቴው አባላት አሳሰቡ፡፡
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ካንፓኒዎች ጋር ተወያዩ።