ኅብረተሰቡ በከተማ አሥተዳደሩ በሰላም፣ በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡

19

ደሴ: ግንቦት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አሥተዳደር ከልዩ ልዩ የልማት ድርጅቶች መሪዎች እና ሠራተኞች፣ ከመንግሥት ተቋማት መሪዎች እና ሠራተኞች ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ዙሪያ በደሴ ከተማ ምክክር እየተካሄደ ነው።

የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ከሕዝብ ፍላጎት በመነሳት በሰላም በልማት እና በመልካም አሥተዳደር የተከናወኑ ተግባራት በደሴ ከተማ በሁሉም ዘርፍ አበረታች ስኬቶች እንዲመዘገቡ አስችሏል ብለዋል። ውይይቱን የመሩት በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) ክልሉ ያለበትን ሁኔታ እና በክልሉ ያጋጠመውን ችግር አንስተው የመውጫ መንገዶችንም አመላክተዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በከተማ አሥተዳደሩ በሰላም በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ላይ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።

ዘጋቢ፡- አንተነህ ፀጋዬ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምክክር ምን መልካም ነገር እንደሚያመጣ ለጎረቤት ሀገራት እና አህጉራችን አፍሪካ ለማሳየት የተዘጋጀንበት ወቅት ላይ ደርሰናል” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
Next article“በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እሴት የተጨመረባቸውን ምርቶች ሀገራችን ለውጭ ገበያ እያቀረበች ነው” የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል