
ባሕር ዳር: ግንቦት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጋራ ገቢዎች አሥተዳደር ክፍፍልና ማስተላለፍን በተመለከተ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሃዋሳ ከተማ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው። በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት እንዲኖር የገቢ ክፍፍልና ማስተላለፍ ቀመር ግልጽና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ መኾን እንዳለበት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል፡፡
አፈ ጉባኤ አገኘሁ ክልሎች እኩል አልያም የተመጣጠነ እድገት እንዲኖራቸው ጠንካራ የጋራ ገቢ አሥተዳደር ሥርዓት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በተለይ የማዕድን እና ትላልቅ ሃብቶች ገቢ አሥተዳደር ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ መተዳደር እንዳለበት አስገንዝበዋል። ኤፍቢሲ እንደዘገበው መንግሥት ለዚህ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!