የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለኅብረተሰቡ በማቅረብ የገበያ መረጋጋት ሥራ እየተሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ።

21

ደሴ: ግንቦት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የ10 ወራት አፈፃፀም ግምገማ እና በቀጣይ አቅጣጫ ዙሪያ በኮምቦልቻ ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው። የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ ቴዎድሮስ ፀጋዬ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ 71 ሺህ ኩንታል የግብርና እና 32 ሺህ ኩንታል የኢንዱስትሪ ምርት ገበያውን ለማረጋጋት በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ተወካይ ኀላፊ መልካሙ አሰፋ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት 7 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በመመደብ ከ 14 ሺህ ኩንታል በላይ የተለያዩ ምርቶችን እና ከ405 ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረቡን ተናግረዋል።

የክልሉ ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሂም ሙሐመድ (ዶ.ር) የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለኅብረተሰቡ ማቅረብ መቻሉን እና በዚህም የገበያ መረጋጋት መፈጠሩን ገልጸዋል። ከዚህ በጀት ውስጥም 678 ሚሊዮን የሚኾነው በተዘዋዋሪ ብድር የቀረበ መኾኑን ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፡- መስዑድ ጀማል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የግንኙነት መድረክ ያላት ተቀባይነት ማደጉ የብሪክስ አባል መኾኗ ለሚያስገኝላት ጥቅም ማሳያ ነው” አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን
Next articleየተጠባባቂ ጥሪ ማስታወቂያ !